ከሚያደርሳቸው ጥቃቶች በተቃራኒ አል-ሸባብ ‘ተዳክሟል’- ባለስልጣናት

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት እ..ኤ.አ. መጋቦት 16 ቀን 2017 ሶማሊያን የጎበኙ ሲሆን በሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ክሄሬ አቀባበል ተደርርጎላቸዋል፡፡

 

የሶማሊያ እና የአጋር መንግስታት ባለስልጣናት የአል-ሸባብ ታጣቂዎች በቅርቡ ጥቃቶችን ቢያደርሱም፣ የአገሪቱ የደህንነት ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑን ገለጹ፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) አዛዥ ፍራንቺስኮ ካይታኖ ሆዜ ማደሪያ ባለፈው ሐሙስ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በቪዲዮ ባደረጉት ንግግር ከአገሪቱ ግዛት ውስጥ 80 በመቶ ያህሉን ከታጣቂው ቡድን አል-ሸባብ መንጠቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

የደህንነት መሻሻሉ የተልዕኮው እና የሶማሊያ ብሔራዊ ኃይል ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከአዛዡ ግምገማ ጋር በመስማማት የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ ፋርማጆ አል-ሸባብ የሶማሊያ እና የአሚሶም ጦር ኃይል አባላት በከፈሉት መስዋዕትነት አል-ሸባብ ተዳክሟል ብለዋል እርሳቸውም በቴሌኮፍንፍረንስ ባደረጉት ንግግር፡፡

ይሁንና ሰፊ ይዞታውን ካጣ በኋላም አልሸባብ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረጉ ድንገተኛ ጥቃቶችን ማድረሱን ቀጥሏል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ታጣቂ ቡድኑ ፖሊስ አስር ሰዎችን ሞተውበታል ላለው ከባድ የሞቃዲሾ ፍንዳታ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡

ፍንዳታው ፈንጂዎችን በጫነ ተሽከርካሪ አማካይነት ቪላ ሶማሊያ እየተባለ ከሚታወቀው ሞቃዲሾ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ መግቢያ በ150 ሜትር ርቀት ላይ የደረሰ ነው፡፡ በመንገዱ ዳር የተለያዩ ቁሳቁሶችን ሲሸጡ የነበሩ በርካታ ሴቶች እንዲሁም የፖሊስ ኃይል አባላት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

C72XcnTXgAAxmW5
የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት አሚሶም ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ በጉብኝታቸው ወቅት ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ (ምንጭ፡- አሚሶም)

ሌላ ቦምብ የያዘ ተሽከርካሪ በሞቃዲሾው የድሃርካነሌይ አካባቢ ባለፈው እሁድ የፈነዳ ሲሆን፣ በዚህኛው ጥቃት ግን ሰው ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ማረጋገጫ የለም፡፡ ቅዳሜ ዕለት በከተማዋ ውስጥ ተኩስ የተዘገበ ሲሆን፣ ይህ አንድ የትምህርት ባለስልጣነ4 ገድሏል፤ የዚህ ጥቃት ፈጻሚ አል-ሸባብ ስለመሆኑ ግን ወዲያውኑ ግልጽ አልሆነም፡፡

የአሚሶም አዛዥ ካይታኖ ሶማሊያ ውስጥ ‘ነጻ የወጡ’ ማህበረሰቦችን ደህንነት ለማረጋገጥ የበለጠ መሠራት እንዳለበት፣ የሶማሊያ ወታደሮችን  ምልመላ እና ትጥቅ ማሻሻል እንደሚገባ እንዲሁም ለጦር ኃይሎቹ ጊዜውን የጠበቀ ክፍያ መፈጸም እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል፡፡ ተልዕኮው እ.ኤ.አ. በ2018 ከአገሪቱ ለመውጣት ዕቅድ እንዳለውና ከዚያ በኋላም የሞቃዲሾ መንግስት ሙሉ በሙሉ በሶማሊያ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር እንዲሆን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፋርማጆ በጦር ጠቅልሎ መውጣት የተስማሙ ሲሆን ለሶማሊያ የጦር ሠራዊቷን እና የደህንነት ኃይሏን የማጠናከር አስፈላጊነት አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡ “ግባችን ይህ ነው፤ በእናንተ ድጋፍም እናሳከዋለ”ን ሲሉ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ተናግረዋል፡፡