የትራምፕ አስተዳደር በሱዳን ላይ የጣለውን  የምጣኔ ሀብት ማእቀብ በቋሚነት  ለማንሳት ውሳኔ ላይ ሊደርስ  የሚገባበት እ.ኤ.አ ሀምሌ  12  ቀን ተቃርቧል።

ከባራክ  ኦባማ የመጨረሻ ክንውኖች መካከል  አስርት አመታትን ያስቆጠረውን እና ዩኤስ  አሜሪካ በሱዳን ላይ የጣለችውን የንግድ ማእቀብ  የሚደመድም  ድንጋጌ ማሳለፍ  ነበር። የኦባማ እርምጃ የሱዳን እና አሜሪካን ግንኙነት የሚያሻሽል  እንዲሁም ሱዳንን በምጣኔ  ሐብት የሚያግዝ ነው በሚል በካርቱም  ተወድሶ ነበር።

ይሁን እንጅ  ድንጋጌው ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው  በሀምሌ ብቻ ሲሆን  እርሱም ሱዳን በአምስት  አካባቢዎች  ወይንም  ዘርፎች ከዩኤስ አሜሪካ ጋር  በምታደርገው  ትብብር ላይ የሚመሰረትም  ነው። ስለዚህም ማእቀቡን የማንሳቱ የመጨረሻ ውሳኔ ኦባማን  በተኩት  ዶናልድ ትራምፕ  እና  ከሌሎች ከፍተኛ  አማካሪዎች  ጋር  በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው በሬክስ  ቲለርሰን  እጅ ላይ ወድቆ ይገኛል።

ሁለት የዜና  ምንጮች  በቅርቡ  እንደዘገቡት ከሆነ የዩኤስ ባለስልጣናት ሱዳን በአምስቱ  ዘርፎች  ባሳየችው  እርምጃ  ዙርያ አዎንታዊ ምልከታ ይዘዋል። ከአምስቱ  ዘርፎችም የሎርድስ ሬዚስታንስ አርሚ (ኤልአርኤ)  የሚያመጣውን  አደጋ  መቆጣጠር፣ በ”ሁለቱ  አካባቢዎች” እና  በዳርፉር  ግጭትን ማስቆም፣  ለዳርፉር  የሰብአዊ እገዛን ማሻሸል እና ሱዳን በጎረቤት  ደቡብ ሱዳን ያላትን ጣልቃ  ገብነት  ማቆም የሚሉት  ይገኙበታል።

በቅርብ የብሉምበርግ ዘገባ “ቁልፍ  ረዳቶችን” በመጥቀስ  ቲለርሰን የመጨረሻውን  ውሳኔ  ገና  ባያሳልፉም ማእቀቦቹን ማንሳትን እንደሚደግፉ  አትቷል።  ኤኤፍፒ በበኩሉ ካርቱም  ውስጥ ያሉ የዩኤስ  ዲፕሎማትን በመጥቀስ ሱዳን በአምስቱ ዘርፎች ያሳየችው እርምጃ “አዎንታዊ” ነው  ማለታቸውን ገልጿል።

አሁን ለትራምፕ አስተዳደር  ያሉ  አማራጮች የኦባማን ውሳኔ ማስቀጠል፣ ድንጋጌውን ሰርዞ  ማእቀቡን ዳግመኛ  ማጽናት፣  የንግድ ማእቀቡን  ብቻ አንስቶ ሙሉውን ማእቀብ  የማንሳቱን ጉዳይ ግን በአምስቱ  የተጠቀሱት አካባቢዎች ተጨማሪ ማሻሻልን በማሳየት ላይ መመስረት ይገኙባቸዋል።

ዘ ሜሴንጀር  ለሁለት  አስርት  አመታት ያህል  ሱዳን ላይ ተጥሎ የቆየውን የንግድ ማእቀብ ለማንሳት የአሜሪካ ባለስልጣናት ማጤን እንደጀመሩ  ታብራራለች።

#1 –  የፀረ ሸብር ትብብር

የዩኤስ መንግስት እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ ዳሬ ሰላም እና ናይሮቢ  የአሜሪካ ኤምባሴዎች  ላይ  ጥቃቶችን ለፈጸሙ  የአልቃይዳ አፈንጅዎች ድጋፍ ሰጥታለች መባሉን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ማእቀብ ከጣለባት ጊዜ  አንስቶ  ሱዳን አሁን እጅጉን የተለየች  አገር ሆናለች።  ከመስከረም አንድ 2001ዱ ጥቃት በኋላ በቅድሚያ በፕሬዚዳንት  ጆርጅ ደብልዩ  ቡሽ  ያንሰራራውና በኋላም  በኦባማ ዘመን የቀጠለው  የፀረ-ሽብር ትብብር ወሳኝ የትብብር  መስክ  ሆኖ  ዘልቋል።

ባለፈው  መጋቢት የሱዳን ጋዜጦች እንደዘገቡት  የአገሪቱ  የደህንነት  አገልግሎት የበላይ ኃላፊ በሲአይኤው   መሪ ማይክ ፖምፒዮ ተጋብዘው ዋሽንግተንን መጎብኝታችውን  ዘግበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ  ሱዳን  የአሜሪካም ጠላት በሆነውና ራሱን ኢስላሚክ ስቴት እያለ በሚጠራው ቡድን ላይ እርምጃዎችን የወሰደች ሲሆን ከእርምጃዎቹም   መካከል  በርካታ አገር በቀል የቡድኑ ደጋፊዎችን ማሰር ይገኝበታል።

ባለፈው  ሳምንት በካርቱም የአሜሪካ  ወኪል የሆኑት ስቲቨን ካውትሲስ ከኤኤፍፒ ጋር ባደረጉት  ቃለ መጠይቅ መጀመሪያ በፕሬዚደንት  ቢል  ክሊንተን የተጣለው  ማእቀብ  ዋነኛ አላማው ሱዳን ለጽንፈኛ  ቡድኖች የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም  ጫና ለማሳደር እንደነበር አስታውሰዋል። ቆይቶም ለዳርፉር ጦርነት በምላሽነት ሌሎች ማጠናከሪያዎች በፕሬዚዳንት ቡሽ ተጨምረዋል።  ዋሽንግተን በካርቱም የሰብአዊ መብቶች አያያዝ  ላይ ልዩነት ቢኖራትም ማእቀቡን የማንሳቱ ጉዳይ ከሰብአዊ መብቶች ጋር  የተያያዘ  መሆን አለበት ብለው አንደማያስቡ ካውትሲስ ተናግረዋል።

#2 – በሁለቱ አካባቢዎች፣ በዳርፉር የጥቃቶችች   ቁጥር ዝቅ  ማለት

ሱዳን በሁለቱ  የደቡብ ኮርድፋን  እና  የብሉ ናይል  አካባቢዎች በ2016-2017 ደረቅ ወቅት  ምንም  አይነት አብይ ጥቃት አልሰነዘረችም። ከዚያ ይልቅ የተኩስ አቁም ስምምነትን ያወጀች ሲሆን እርሱም የተቋረጠው በአንዳንድ አጥቢያዊ የፍልሚያ ክስተቶች ብቻ ነው። በከፊል ክርስትያናዊ በሆኑ አካባቢዎች አነስተኛ  ግጭቶች መኖራቸው  የሃይማኖት ነፃነት  ጉዳይ ለሚያሳስባቸው  የዋሽንግተን ባለስልጣናት ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው።

በመጋቢት ወር  የተጠናቀቀው  የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት  ጥምር የዳርፉር ሰላም ማስጠበቅ  ተልእኮ ቅኝት  እንደሚለው ከሆነ የዳርፉር የጸጥታ ሁኔታ በከፊል ተሻሽሏል። መንግስቱ  እና በርካታ አማጺ ቡድኖች  የተኩስ አቁም  ስምምነቱን በአብዛኛው  አክብረዋል። ሆኖም በ ግንቦት ወር የኤስኤልኤም-ሚኒ  ሚናዊ አማጺ  ቡድን ሀይሎች ከደቡብ ሱዳን ከተባረሩ በኋላ ከመንግስት ጋር ተጋጭተው ተሸንፈዋል።

የመጨረሻው አብይ የመንግስት ጥቃት የደረሰው ከየካቲት እስከ  ሰኔ 2016 ድረስ  በሱዳን ነፃነት ንቅናቄ-አብደልዋሂድ (ኤስኤልኤም-ኤደብልዩ) ላይ  ጀበል መራ በተሰኝው ስፍራ ነበር። በህዳር ቶሮ ተብለው  የሚታወቁ ከፍተኛ የኤስኤልኤም-ኤደብልዩ ወታደራዊ አዛዥ ከአስርት ተዋጊዎቻቸው እና የቡድኑን ቃል አቀባይ ሺሃባልዲን አህመድ ሃገርን ጭምሮ ከሌሎችም አማጺ የጦር መኮንኖች ጋር  ቡድኑን ትተው መንግስትን ተቀላቅለዋል።

ስለዚህም የኤስኤልኤም-ኤደብልዩ ጠንካራ ይዞታ  የሆኑት  የዳርፉር  ተራራማ ማእከላዊ አካባቢዎች በእጅጉ የቀነሱ ሲሆን ይህም  ከዚያ  በፊት ተቋርጦ  የነበረው እርዳታ ወደአካባቢው እንዲዳረስ መንገድ  ከፍቷል።

# 3  –  ሰብዐዊ  አቅርቦት

32882227233_1f9a2189c9_k
Displaced people at a clinic for medical care in East Darfur, March 2017 (Credit: UNAMID / Abdulrasheed Yakubu)

ባለፉት ስድስት  ወራት የአሜሪካው የእርዳታ ድርጅት  ዩኤስኤአይዲ ሱዳን በምእራባዊ ዳርፉር ክልል ለእርዳታ ድርጅቶች  የሰብአዊ እርዳታን እንዲያዳርሱ ሁኔታዎችን በማሻሻል ሱዳን ያሳየችውን እምርታ  ደጋግሞ አመላክቷል። እ.ኤ.አ ባለፈው አመት  መገባደጃ ላይ የእርዳታ ድርጅቶች በመካከለኛው ዳርፉር  በምትገኘው ጎሎ አገልግሎታቸውን እንደገና መስጠት ጀምረዋል።  የአሜሪካው የእርዳታ ድርጅት ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮር በአካባቢው  አንዳንድ   የጤና አገልግሎቶችን ማቅረብ ጀምሯል።

ከዚህም  ባሻገር  ዩኤስ ባለፈው  ጥር ሱዳን ከዚያ ቀደም በሰብአዊ እርዳታ  ላይ ተጥለው የነበሩ ክልከላዎች  ላይ ያደረገችውን ማሻሻያ በአዎንታ ተቀብላዋለች። “እነዚህ የተከለሱ ደንቦች ተግባራዊ ሲሆኑ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ለመድረስ  የሰብዐዊ እርዳታ አቅራቢ አካላት ጥረታቸውን እንዲያቀላጥፉ  ያስችላል።  ይህንን  እንደአዎንታዊ እርምጃ የምናየው ሲሆን በሰብዐዊ እርዳታ አቅርቦት  ረገድ ዘላቂ  ተጠቃሚነትን እንጠብቃለን”  ብለዋል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ  ቤት ቃል አቀባይ”

#4 – የካታር ቀውስ

በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው  ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ  ዋሽንግተንን  አስቸጋሪ  አጣብቂኝ  ውስጥ  ዘፍቋታል።  ካታር፣  ሳዑዲ አረቢያ  እና ዩናይትድ  አረብ  ኤምሬትስ  ሶስቱም የአሜሪካ  ወዳጆች  ሲሆኑ ዋሽንግተን ውስጥ ሁሉም የየራሳቸው  ፖለቲካዊ  ውትወታ  ከዋኞችና የየራሳቸው የተጽእኖ   ነጥቦች  አሏቸው። የሬክስ  ቲለርሰን  የውጭ  ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት  በገልፍ  አገራቱ  መካከል የተራዘመ እና አካባቢውን የሚያተራምስ የሃይል  ፍትጊያ  እንዳይፈጠር የሚያስችል  አጣዳፊ መፍትሄ  ማግኘት ይፈልጋል።  ግን ደግሞ ቲለርሰን በሳዑዲ መራሹ ጥምረት የቀረቡትን  ጥያቄዎች  እንዲሁ በቀላሉ ማጣጣልና የበለጠ  ሃያል የሆነውን የመካከለኛው  ምስራቅ ወዳጆች  ቡድን የሚመሩትን ሳዑዲዎችን ማግለል  የሚያዋጣቸው  አይሆንም።

የካታሩ ቀውስ  በሱዳን የማዕቀብ ውሳኔ  ላይ “ዋጋውን  ከፍ ያደርጋል።”

ይህ ማለትም በመጭዎቹ ሳምንታት ዋሽንግተን የካታርን ቀውስ መፍትሄ ለማግኘት  ስትጥር ከሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው  ምስራቅ  ሱኒ አረብ ሃይሎች-ሱዳን ከመካከለቸው አንደኛዋ ናት-ጋር ያላትን ግንኙነት በተመለከተ  በጥንቃቄ የመራመድ  አዝማሚያ  ሊኖራት ይችላል። የሱዳንን  ማዕቀብ ማርገብ በሱዳን ብቻ ሳይሆን ምናልባትም በቀረው የመካከለኛው ክፍል ሁሉ በበጎ  ሊታይ  ይችላል።

የቀድሞ የዩኤስ  ከፍተኛ  ባለስልጣንና በደቡብ ሱዳን ጉዳይ የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት የባለሞያዎች ፓናል አስተባባሪ የነበሩት ፓይተን ኖፕፍ እንደሚሉት  ከካታር ቀውስ  ጋር የተገጣጠመው የሱዳን ማዕቀብ የሀምሌ  ቀነ ገደብ የውሳኔውን “ከፍ ያደርገዋል።” እ.ኤ.አ ሰኔ 21 ቀን በትዊትር  አድራሻቸው  ላይ ሲጽፉ  ኖፕፍ  ሳዑዲ አረቢይ በሱዳን ላይ  የተጣለው  ማዕቀብ እንዲነሳ ስትወተውት መቆይቷን አውስተዋል።

#5 – ከሎርድስ ሬዚስታንስ አርሚ ጋር የሚደርገውን ፍልሚይ ማስቆም

ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እና አጋሯ ዩጋንዳ በማዕከላዊ አፍሪካን ሪፐብሊክ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለረጅም ጊዜ ያህል  ከሎርድስ ሬዚስታንስ አርሚ ጋር ሲደርግ የቆይውን  ፍልሚያ በአስፈላጊነት ቅድመ ዝርዝራቸው ላይ ዝቅ  አድርገውታል። የዩኤስ ልዩ ሃይሎችና የዩጋንዳ ወታደሮች የኤልአርኤውን መሪ ጆሴፍ ኮኒን ፍለጋ  በባዶ እጅ አቋርጠው ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሚያዝያ ወር ወጥተዋል።

ቀደም ሲል ኮኒ  መቀመጫውን ርቆ በሚገኘው የሱዳን ካፊያ  ኪንጂ አካባቢ እንዳደረገ ተዘግቦ  የነበረ ቢሆንም  አሁን ያለበት ቦታ ግን አይታወቅም። በትብብር የተንቀሳቀሱት   የጦር ሃይሎች የኤልአርኤን  መናገሻዎች ለማጥፋት ከጣሩ፣   የአማፂ ቡድኑ ወታደሮች እንዲከዱ ካበረታቱና ቁልፍ መሪዎችን ከያዙ በኋላ የኮኒ  ተከታዮች  ቁጥራቸው  ወደ150 ዝቅ ብሏል ይላሉ የዩኤስ የአፍሪካ  እዝ (አፍሪኮም) መሪ ጄኔራል ቶማስ ዋልድሃውዘር።

“ኤልአርኤ   ለማዕከላዊ መንግስታትና ለህዝብ መኖሪያ  አካባቢዎች ስጋት አይደለም፣ አስተዳደር ለሌለባቸው አነስተኛ  ስፍራዎች  እንጅ” ብለዋል ዋልድሃውዘር በመጋቢት ወር ለዩኤስ ሴኔት በሰጡት ቃል።
የኤልአርኤ ወታደሮች በቅርብ በ2016 ዳርፉር ውስጥ መታየታቸው የተዘገበ ቢሆንም አንዳንድ ምዕራባዊ ተንታኞች ግን  ሱዳንን እንደአዋኪ ሳይሆን  አጋር ልትሆን እንደምትችል አገር ነው የሚያዩዋት።  ሃሳብ አመንጭው ኢንተርናሸናል ክራይሲስ  ግሩፕ  በአዲስ ሪፖርቱ “ካርቱም  ራሷን ከኤልአርኤ እንዳደረገገች ነው የሚታመነው” ብሏል። ሃሳብ አመንጭ ቡድኑ ሱዳን  በ2017  ኤልአርኤን ለማጥፋት ትብብርን ለማቀላጠፍ የተደረገ  አካባቢያዊ ስብሰባ ላይ መሳተፏን አማፂውን  ቡድን  ለማጥፋት  በአሜሪካ መሪነት ለሚደረገው  ጥረት  ያላትን “የተባባሪነት ፈቃድ”  አመላካች ነው  ሲል ጠቅሶታል።

በቅርብ ወራት ውስጥ ኤልአርኤን ለማሳደድ የተሰጠው  ዝቅ ያለ አትኩሮት ፣  ሱዳን ቡድኑ ላይ ላነጣጠሩ እርምጃዎች ተባባሪነትን እያሳየች እንደሆነ ከመታመኑ ጋር ተዳምሮ  የተጣለባትን ማዕቀብ እንዲነሳላት የዩኤስ  ባለስልጣናት ሲመዝኑ ሊጠቅማት  ይችላል።

Categories: Amharic News

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *